ጳጉሜን-3 የበጎነት ቀን "በጎነት ለሃገር!"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማለዳ 424ሺህ 689 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ፣ የሀገር ባለውለታዎች እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሠራተኞች አዲሱን ዓመት በደስታ እንዲቀበሉ ማዕድ በማጋራት የበጎነት ቀንን አስጀምረዋል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን የነዋሪውን ዕርስ በዕርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባሕል እንዲጎለብት አድርገናል ያሉ ሲሆን ዛሬ ለነዋሪዎቻችን የምናጋራው ማዕድ ብቻ ሳይሆን አብሮነትንና ፍቅርንም ነው ብለዋል::

ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ልበ-ቀና ባለሀብቶች ከንቲባ አዳነች አቤቤ በነዋሪዎች ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Share this Post