11
Sep
2023
"የከተማችን የባሕል ኪነጥበብ ከያንያን ፣ የኢቢሲ ሴት ጋዜጠኞችና የሽኖዬ ባሕል ቡድን በጽህፈት ቤታችን ተገኝተው እንደ ወግ ባሕላችን አበባአየሽወይ እና ሽኖዬ ተጫውተው አዲሱ ዓመት የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ስለተመኙልን አመሰግናለሁ።
የሁላችን መልካም ቤት በሆነችው አዲስ አበባ፣ ህብረታችንን እያፀናን በአዲሱ ዓመት ከነዋሪዎቻችን ጋር በመሆን በጋራ እያቀድን በመተባበር ለመኖር ምቹ የሆነች አዲስ አበባን መገንባታችንን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
መልካም አዲስ አመት!"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ