11
Sep
2023
"ኢትዮጵያ የትውልዶች ድምር!" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው ጳጉሜ-5፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ብዜና አልቃድር 4000 ሺህ በላይ መፅሐፍ ለአብሮሆት ቤተ መፅሐፍ በስጦታ አበረከቱ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልቀድር የትውልድ ቀንን ምክንያት በማድረግ በአብሮሆት ቤተ መፃሕፍት ለህፃናት የመደመር ትውልድ መፅሐፍንም አንብበዋል፡፡
የራስን ህብረተሰብ በጥልቅ ዕውቀትና በሀሳብ ምንጭነት ኮትኩቶ በራሱ እንዲቆም ማድረግ አስፈላጊ ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ የዕውቀትን ዋጋና ትርጉም የተረዳ ትውልድ መፍጠርም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
አፈ-ጉባኤዋ አክለውም፣ የመደመር ትውልድ የአዳዲስ ሐሳቦችና ቴክኖሎጂዎች አፍላቂ የሆነ ትውልድ መገንባት ፤ በሥነ ምግባርና የትጋት የታነፀ ትውልድ መፈጠር በየደረጃው ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን የትውልድ ቅብብሎሽ ጥልቅ መሰረት ያለው ሕዝብና ሀገር ለመገንባትና ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስከበር በዕውቀት ራሱን መቻል እጅግ አስፈላጊ ነውም ብለዋል።