ጳጉሜን-1 የአገልጋይነት ቀን

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀውን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ፤

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአገልግሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

የከተማዋን ነዋሪ በወሳኝ ኩነቶች (Vital Events) ለ80 ዓመታት ሲያገለግል የኖረው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በዛሬው እለት ያስመረቀው የዋና መስሪያ ቤቱ ህንፃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ሲሆን የሃገሪቱን የሲቪል ምዝገባ ስርዓት እና የዲጂታላይዜሽን ስራ የደረሰበትን ደረጃ ሊያሳይ በሚችል መልኩ ተገንብቷል፡፡

በሰው ኃይል፣ በአደረጃጀትና እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው ኤጀንሲው ከዋና መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ በዛሬው እለት በ33 ወረዳዎች በቴክኖሎጂ በተደገፈ ሁኔታ አገልግሎት የሚሰጡ ፅ/ቤቶቹን አስመርቆ ለኘገልግሎት ክፍት አድርጓል።

Share this Post